መልእክት
2026-11-29 12:28:51
እንኳን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መረብ ገጽ በደህና መጡ! የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአዳማ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ ሲሆን፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊ እና የህዝብ ፍላጎትን ያማکለ አገልግሎት በመስጠት የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ዋና ዓላማችን መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ፣ የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር፣ የመንግስት አገልግሎቶችን ማዘመን፣ የስራ እድል መፍጠር፣ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ማስፋፋት እና ቦሌ ክፍለ ከተማን ለኑሮ፣ የስራ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ ነው። በተለይም የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በመቀየር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማዕከላትን በማዘመን እንዲሁም የስማርት ከተማ (Smart City) ጅምሮችን ስራ ላይ በማዋል የህዝብ አገልግሎትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር እየሰራን እንገኛለን። ይህ መረብ ገጽ የመንግስት መረጃዎችን በግልጽነት ለህዝብ ለማድረስ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለመስጠት፣ የህዝብ አስተያየት እና ቅሬታዎችን ለመቀበል እንዲሁም የመንግስት እና ህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የተዘጋጀ ነው። የእኛ ስኬት በህዝባችን፣ በባለሀብቶች፣ በመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት ሁሉ ተሳትፎ እና ትብብር ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም ዘመናዊ፣ አረንጓዴ፣ ንጹህ፣ ሰላማዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቦሌ ክፍለ ከተማን ለመገንባት ሁላችንም በጋራ እንድንሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ። በአንድነት እንለማለን፣ በቴክኖሎጂ እንዘምናለን፣ በአገልግሎት እንሳካለን!